የአፍሪካ ሴት የትምህርት ባለሙያዎች ፎረም (FAWE) ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የማስተርካርድ ፋውንዴሽን ፕሮግራምን ተግባራዊ አድርጓል። ይህ ፕሮግራም ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች ባሉ 10 የአፍሪካ አገሮች ከ 2016-2022 ዓ.ም ተግባራዊ ይሆናል።
የፕሮግራሙ ምእራፍ 2 ትግበራ ትኩረት በዝቅተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ የሚገኙ እድሜያቸዉ ከ 15-25 የሆኑ ወጣት የህብረተሰብ ክፍሎችን ነገር ግን በትምህርት ክህሎታቸዉ የተሻለ ውጤት ያላቸውን የከፍተኛ ትምህርት ዕድሎችን በሙያ እና ቴክኒክ ስልጠና ተደራሽ በማድረግ ወጣቶች በተለይም ሴቶች በተሳካ ሁኔታ ወደ ሥራ ዓለም እንዲሸጋገሩ ማገዝ ነው።
ፋዌ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሰባት ዓመታት (2024-2030 እ.ኤ.አ) በማስተርካርድ ፋዉንዴሽን ምዕራፍ 2 ፕሮግራም አማካኝነት 800 ወጣቶችን ለማገዝና እና ለማብቃት ይሰራል፣ ከነዚህም ዉስጥ 80% የሚሆኑት ሴቶች እና 20% ወንዶች ሲሆኑ ከ5%-10% የሚሆኑት አካል ጉዳተኞች፣ ከ10%-15% የሚሆኑት በሃገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎችን እና የውጭ አገር ዜጎች ስደተኞችን ያካትታል፡፡
ፕሮግራሙ ተግባራዊ የሚደረገዉ በአዲስ አበባ፣ በአማራ ክልል፣ በኦሮሚያ ክልል እና በሲዳማ ክልል ነው።
አመልካቾች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ትምህርት ለመግባት ፍላጎቱ እና ቁርጠኝነት ያላቸው መሆን አለባቸው።
በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ፕሮግርማኡ በሚተገበርባቸው አራት ክልሎች ማለትም በ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ በኦሮሚያ ክልል(አዳማ ከተማ) ፣ በ አማራ ክልል (ባህርዳር ከተማ) እና በሲዳማ ክልል(ሃዋሳ ከተማ) በድምሩ ለ 208 ወጣት ተማሪዎች የትምህርትና ስልጠና ድጋፉ ተመቻችቷል።
በኢትዮጵያ ፋዌ የትምህርት እና ስልጠና ድጋፍ ሊያገኙ የሚችሉ እነማን ናቸው?ሁሉም ለቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ስኮላርሺፕ የሚያመለክቱ አመልካቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡:
|
አመልካቾች በታች በተዘረዘሩት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ውስጥ በመደበኛው ፕሮግራም ለመማር ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡![]() |
እንዴት ማመልከት እንደሚቻል
የማመልከቻ ቅፆች ያለምንም ወጪ ከላይ በተዘረዘሩት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማት የአካዳሚክ ሬጅስትራር ቢሮዎች ይገኛሉ።
- የተሞላውን ማመልከቻ ፎርም እና ማስረጃዎችን በመሰብሰብ ከላይ በተጠቀሱት ተቋማት ያቅርቡ።
- የማመልከቻው ቀናት ከ ———- ፤ 2018 ዓ.ም ሲሆን ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጭ የሚመጣ ማመልከቻ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- የምርጫዉን ሂደት ፋዌ ኢትዮጵያ በሚመራዉ ገለልተኛ በሆኑ የወረዳ፣ ክልል እና ሀገር አቀፍ የተማሪዎች መራጭ ኮሚቴ የሚከናወን ይሆናል
- ወደ ፕሮግራሙ ለመግባት ያመለከቱት አመልካቾች ያቀረቡት ሁሉም የማስረጃ ሰነዶች እውነተኛነታቸውን የማረጋገጥ ስራ የሚሰራ ሲሆን ፣ የሚኖሩትን የምልመላ ደረጃዎች በተሳካ ሁኔታያለፉ አመልካቾች ብቻ እንዳለፉ እንዲያውቁ ይደረጋል
- ይህ የትምህርት እና ስልጠና ድጋፍ ፕሮግራም ለፕሮግራሙ ተሳታፊ ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ጊዜ የሚስፈልጋቸውን ሁሉን አቀፍ የሆነ የገንዘብ፣ የትምህርት እና ስልጠና እንዲሁም የማህበራዊ ድጋፍን ያካትታል።
- ፋዌ ኢትዮጵያ በማንኛዉም ሰራተኛ፣ አማካሪዎች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ወይም ከ ፋዌ ኢትዮጵያ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ትግበራ ጋር በተያያዘ የስራ ግንኙነት ባላቸዉ ማንኛውም ግለሰቦች እና አጋሮች አማካኝነት የሚፈፀሙ የልጆች ጾታዊ ጥቃትን፣ ብዝበዛን እና ጾታዊ ትንኮሳን በተመለከተ ምንም አይነት (ዜሮ) መቻቻል ሊሲ ይከተላል
